የዓመት ዕረፍት እና በሳምንታዊና በህዝብ በዓላት መስራት

This page was last updated on: 2021-03-19

ከክፍያ ጋር ዕረፍት/ አመታዊ ፈቃድ

ለመጀመሪያ አንድ የአገልግሎት ዓመት ሠራተኞች 16 የሥራ ቀናት እንዲሁም ከአንድ ዓመት በላይ ለተበረከተ አገልግሎት ለእያንዳንዱ ሁለት የአገልግሎት ዓመታት አንድ የሥራ ቀን እየተጨመረ የዓመት ፈቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጣል፡፡ 5 አመት አገልግሎት ያለው ሰራተኛ 18 የሥራ ቀናት ከክፍያ ጋር የዓመት ፈቃድ ያገኛል (1 ተጨማሪ ቀን በየሁለት ዓመት)፡፡

ቀጣሪው በሚያዘጋጀው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ሰራተኛው ከፈለገ/ገች እና መደበኛ ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ አስፈላጊ ሲሆን አንድ ሠራተኛ የመጀመሪያውን የዓመት እረፍት ከአንድ ዓመት አገልግሎት በኋላ የመውሰድ መብት ሲኖረው ቀጣዩንና ተከታታዮቹን በእያንዳንዱ የካሌንደር ዓመት ውስጥ ሊወስድ ይችላል፡፡  አንድ ሠራተኛ በአሰሪው ፍቃድ እረፍቱን በሁለት በመክፈል ለመውስድ ወይም እስከ ሁለት ዓመት ድረስ እንዲያስተላልፍለት አሰሪውን ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ለውጥ ሁለት ተከታታይ አመታት ሊበልጥ አይችልም፡፡

አንድ ሰራተኛ የአመት ፍቃድ መብቱን ሳይጠቀም የስራ ውሉ ቢቋረጥ በአገልግሎት ዘመኗ/ኑ ርዝማኔ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የእረፍት ማካካሻ ይደረግለታል/ላታል፡፡ ከዚህ ድንጋጌ በተጨማሪ ለአመት እረፍት ማካካሻ የሚሰጥ ወይም የሚከፈልበት የአመት እረፍት መብትን የሚሽር ወይም የሚሰርዝ ወይም የሚያስቀር ማንኛውም ስምምነት፣ የህብረት ስምምነት ወይም ሌላ ስምምነት የተሻለ እና ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ አንድ ሰራተኛ በአመት እረፍቱ ጊዜ ቢታመም ከህመም ፍቃድ ጋር ግንኙነት ያላቸው ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ የአመት እረፍት ሊቋረጥ የሚችል ሲሆን አሰሪው በአመት እረፍት ላይ ያለን ሰራተኛ መጥራት የሚችለው ያልታሰቡ ሁኔታዎች ተከስተው የሰራተኛውን በስራው ላይ መገኘት ሲያስፈልግ ብቻ ይሆናል፡፡ ከእረፍት ላይ የተጠራ ሰራተኛ በጉዞ ላይ ያጠፋውን ሰዓት ሳይጨምር የቀሪ እረፍት ጊዜውን የሚሸፍን ክፍያ የማግኘት መብት ያለው ሲሆን አሰሪው ሰራተኛው በመጠራቱ ምክንያት በቀጥታ ለሚያጋጥመው ወጪ ሁሉ እና ውሎ አበል ወጪዎችን መሸፈን ይኖርበታል፡፡

ምንጭ፡ የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 77-79

በህዝባዊ በዓላት ወቅት ክፍያ

ሰራተኞች ክብረ በዓላት /ህዝባዊ እና ሀይማኖታዊ/ ወቅት ከሙሉ ክፍያ ጋር ዕረፍት የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ይህም መታሰቢያ እና ሀይማኖታዊ /ክርስቲያንና ሙስሊም/ በዓላትን ይጨምራል፡፡ ህዝባዊ በዓላት አብዛኛውን ጊዜ በቁጥር 13 ናቸው፡፡- እነዚህ ቀናት ገና (ታህሳስ 29)፣ የነቢዩ መሐመድ ልደት (መውሊድ)፣ ጥምቀት (ጥር 11)፣ የአድዋ ድል (የካቲት 23)፣ ስቅለት (ሚያዝያ 10)፣ ትንሣዔ (ሚያዝያ 12)፣ ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን (ሚያዝያ 23)፣ የኢትዮጵያ አርበኞች መታሰቢያ (ሚያዝያ 27)፣ የደርግ መንግስት የወደቀበት (ግንቦት 20)፣ ኢድ አልፈጥር ረመዳን፣ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት (መስከረም 1)፣ መስቀል (መስከረም 17) እና ኢድ አል አድሐ/አረፋ ናቸው፡፡ (የሙስሊም በዓላት በጨረቃ ካላንደር መሠረት ናቸው)፡፡

አንድ የሕዝብ በዓል ከሌላ የሕዝብ በዓል ጋር ቢደረብ ወይም በሕግ በተወሰነ የዕረፍት ቀን ላይ ቢውል በዚህ ቀን የሠራ ሠራተኛ ክፍያ የሚደረግለት በአንዱ የሕዝብ በዓል ብቻ ይሆናል፡፡

ምንጭ፡ የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 73-75፣ በ1975 የወጣው እና በ1996 የተሻሻለው የህዝባዊ ክብረ በዓላት እና እረፍት ቀናት አዋጅ፡፡ 

ሳምንታዊ የዕረፍት ቀን

ሰራተኞች በሳምንት ለ24 ተከታታይ ሰዓታት እረፍት የማግኘት መብት አላቸው፡፡ የአሰሪና ሰራተኛ ህግ ሳምንታዊ የእረፍት ቀን በመርህ ደረጃ ለሁሉም ሰራተኞች እሁድ መሆን እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ በስራው ባህሪ ምክንያት ሳምንታዊ የእረፍት ቀን እሁድ ላይ መስጠት የማይቻል ከሆነ ሌላ ቀን እንደ ሳምንታዊ የእረፍት ቀን በምትክ ይሰጣል፡፡ ሳምንታዊ የእረፍት ቀን ከጠዋቱ 12፡00ሰዓት እስከ ቀጣዩ ቀን 12፡00ሰዓት ጠዋት ያለውን ጊዜ ይጨምራል፡፡ የስራው ባህሪ ወይም በአሰሪው የሚሰራው አገልግሎት ባህሪ በእሁድ ቀን የሳምንት እረፍት የማያሰጥ ከሆነ ሌላ ቀን እንደ ሳምንታዊ የእረፍት ቀን በምትክነት ሊሰጥ ይችላል፡፡

ምንጭ፡ የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 69

ስራና በዓላትን የተመለከቱ ደንቦች

  • የአሰሪና ሰራተኛ ዓዋጅ ቁ. 377/2003 / Labour Proclamation No.377/2003
loading...
Loading...